Monday, May 14, 2018

በትናንቱ ተቃውሞ 55 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል

የእስራኤል ወታደሮች 55 ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞችን ከገደሉ ከአንድ ቀን በኋላ ፍልስጤማውያን ለተጨማሪ የተቃውሞ ሰልፍ እየተዘጋጁ ነው።
ዛሬ እስራኤል እአአ በ1948 ከተመሰረተች 70 ዓመት ታስቆጥራለች። ፍልስጤማውያን ይህን ቀን 'ናክባ' ወይም መቅሰፍት ሲሉ ይጠሩታል።
ትናንት የተገደሉት ፍልስጤማውያን የቀብር ስነ ስርዓታቸው ዛሬ ጋዛ አካባቢ የሚፈጸም ሲሆን በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት ይነግሳል ተብሎ ይጠበቃል።

አሜሪካ አነጋጋሪ የሆነውን ኤምባሲዋን በእየሩሳሌም ከከፍተች በኋላ ነበር ተቃውሞው የተቀሰቀሰው። ይህ የአሜሪካ ውሳኔ በበርካታ እስራኤላውያን ዘንድ ድጋፍ ተችሮታል። ፍልስጤማውያን ምስራቅ እየሩሳሌም የመጻኢቷ ፍልስጤም ዋና ከተማ ናት ብለው ያምናሉ።
የፍልስጤም ባለስልጣናት በትናንትናው ዕለት የተጎጂዎች ቁጥር 2,700 መድረሱን አስታውቀዋል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤናያሚን ኔታኒያሁ በበኩላቸው ጦራቸው እስራኤልን ለማጥፋት ከሚፈልገው ሃማስ እራሱን እየተከላከለ ነበር ብለዋል።
በጋዛ ድንበር ላይ ምን ተፈጠረ?
አሜሪካ አነጋጋሪ የሆነውን ኤምባሲዋን በእየሩሳሌም ለመክፍት ማቀዷን ተከትሎ የዶናልድ ትራምፕ ሴት ልጅ ኢቫንካ እና ባለቤቷን ጃርድ ኩሽነርን ጨምሮ የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በዝግጅቱ ላይ ለመገኘት እስራኤል ገብተው ነበር።
የአሜሪካ ውሳኔ እስራኤላውያንን ቢያስደስትም በርካታ ፍልስጤማውያንን ግን ያስቆጣ ነበር።
በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እስራኤልንና የጋዛ ሰርጥ ድንበር አካባቢ ለተቃውሞ ተሰባሰቡ።
እስራኤል እንደምትለው ከሆነ በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ወደ 40ሺ የሚጠጉ ፍልስጤማውያን በ13 ቦታዎች ላይ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።
የእስራኤል መከላከያ ሃይል ቃል አቀባይ ''ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጪስ በመተኮስ ለመበተን ሞክረናል። በሽብር እንቅስቃሴ ላይ በነበሩት ላይ ግን የእስራኤል ጦር ተኩስ ከፍቷል'' ብለዋል።
የዓለም አገራት ምላሽ ምን ነበር?
  • የአሜሪካ: የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ "ለዚህ ሁሉ ሞት ተጠያቂው ሃማስ ነው. . .'' ብለዋል።
  • የአውሮፓ ህብረት እና እንግሊዝ፡ ሁሉም እንቅስቃሴያቸውን እንዲገቱ ጥያቄ አቅረበዋል።
  • ጀርመን፡ እስራኤል እራሷን የመከላከል መብት እንዳለት በመጥቀስ የምትወስዳቸው እርምጃዎች ተመጣጣኝ እንዲሆኑ ጠይቃለች።
  • ፈረንሳይ፡ ፕሬዝድንት ኢማኑኤል ማክሮን የእስራኤል ጦር በተቃዋሚዎች ላይ የወሰደውን እርምጃ አውግዘዋል።
  • ቱርክ 'ለጭፍጨፋው' አሜሪካ እና እስራኤል ተጠያቂ ናቸው። ለዚህም የሁለቱን አገራት አምባሳደሮች ለማነጋገር ጠርቻለው ብላለች።
  • የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ዛይድ ራዓድ ''በርካቶችን የቀጠፈ አስደንጋጭ በእስራኤል የተፈጸመ ግድያ'' ብለዋል።
  • ደቡብ አፍሪካ ድርጊቱን በመኮነን በእስራኤል የደቡብ አፍሪካ አምባሳደርን ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ አዛለች።
የኤምባሲው መዛወር ለምን አነጋጋሪ ሆነ?
የእየሩሳሌም ሁኔታ የእስራኤል እና የፍልስጤምን ግጭት ሊያባብሰው ይችላል።
እስራኤል የእየሩሳሌም ግዛት ይገባኛል ጥያቄ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባለማግኘቱ።
በ1993 የእስራኤልና የፍልስጤማውያን የሰላም ስምምነት ምንም እንኳን እስራኤልም ባትስማማበትም እየሩሳሌም ሁለት መቶ ሺህ ለሚደርሱ አይሁዶች መኖሪያ መገንባቷና ይህም በአለም አቀፉ ህግ ተቀባይ ባለመሆኑ።
እንዲሁም በርካታ የአለም አገራት ኤምባሲያቸውን በእየሩሳሌም ይሁን እንጂ እንደ አውሮፓውያኑ 1980 በኋላ ወደ እስራኤል እያዛወሩ በመሆናቸው ነው።
                                                                                                 ምንጭ፡- ቢቢሲ.ኮም

No comments:

Post a Comment