Sunday, May 13, 2018

በጀርመን ቡንደስሊጋ ሀምበርግ እግርኳስ ክለብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለተኛው ዲቪዚዮንን ተቀላቀለ፡፡


በጀርመን ሀምበርግ እግርኳስ ክለብ ቡንደስሊጋው ከተጀመረ ከ1963 እ.አ.አ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለተኛ ዲቪዚዮንን ተቀላቀለ፡፡
ሀምበርግ እግርኳስ ክለብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቡንደስሊጋ ወረደ

የመጨረሻ ጨዋታቸውም ደጋፊዎች ወደሜዳ በወረወሩት ቀይ ነበልባል እና ከተቃራኒ ቡድን ጋር በፈጠሩት ግርግር 15 ቂቃዎች እየቀሩት ተጠናቋል፡፡ 

ጨዋታው ደጋፊዎች ወደሜዳ በወረወሩት ቀይ ነበልባል ተቃርጧል
ሀምበርገሮች ቦርስያ ሞንቸንግላባችን የ2ለ1 በያሸንፉም ወራጅ ቀጠና የሚገኘውን ኮሎኝ ወልፍስበርግ 4ለ1 ስላሸነፈ ቦንደስሊጋውን ሊሰናበቱ ተገደዋል፡፡ ሀምበርግ በአንድ ወቅት የአውሮፓ ሻምፒዮን ዛሬ ግን የቦንደስሊጋው ወራጅ ክለብ ሆኗል፡፡

ከቦርስያ ሞንቸንግላባች ደጋፊዎች ጋር በፈጠሩት ግርግር ምክንያትም ጨዋታው ሊጠናቀቅ 15 ደቂቃ ሲቀረው ተቋርጧል፡፡
በቀጣይ ዓመት ሀምበርግ እና ኮሎኝ በሁለተኛው ዲቪዚዮን ይገናኛሉ፡፡ የወልፍስበርግ እግርኳስ ክለብ የቦንደስሊጋ ቆይታ በደርሶ መልስ ጨዋታ የሚወሰን ይሆናል፡፡


የደጋፊዎችን ረብሻ በርካታ ፖሊሶች በፈረስ ሰልፍ እና በሌሎችም ድርጊቶች ለማብረድ ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም፡፡ በዚህም ምክንያት የመሀል ዳኛ ፌሊክስ ብሬይች ጨዋታው ሊጠናቀቅ 15 ደቂቃ እየቀረው የማጠናቀቂያውን ፊሽካ ለመንፋት ተገደዋል፡፡

በጨዋታው ቦቢ ውድ በ71ኛው ደቂቃ በቀይ ወጥቷል፡፡
                                              ምንጭ፡- ሜይል ኦንሊይን

No comments:

Post a Comment