Thursday, May 31, 2018

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአንዳርጋቸው ጽጌ ጋር ቆይታ አድርገዋል

ላለፉት 4 ዓመታት በእስር ላይ ከቆዩት እና ክሳቸው ተቋርጦ በዚህ ሳምንት ከእስር ከተለቀቁት የግንቦት 7 አመራር ከነበሩት እንዳርጋቸው ፅጌ ጋር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቆይታ እንደነበራቸው የሚያሳይ ምስል ፅህፈት ቤታቸው በፌስ ቡክ ገፁ የለቀቀውን ምስል እንዲህ አጋራችሁ፡፡

Sunday, May 27, 2018

ሳይነስን ለማከም 5 ቀላል መንገዶች …

በሳይነስ ለተሰቃዩ ሰዎች ይድረስ… ሼር አድርጓቸው፡፡

ሳይነስ – በሰውነታችን ውስጥ ያሉ አየር የሚንሸራሸርባቻን ክፍሎች የሚያጠቃ የህመም ዓይነት ነው፡፡

ህመሙ ሶስት ደረጃዎች ያሉት ሲሆን፣ አኪዩት፣ሰብ አኪዩት እና ክሮኒክ ሳይነስ(ሲኖሳይተስ) በመባል ይታወቃሉ፡፡

Friday, May 18, 2018

የፎቶ ጋዜጠኝነት ዋጋ!!!?


አንዱ ፎቶግራፈር ባነሳው ፎቶግራፍ ተፀፅቶ ራሱን ሲያጠፋ ሌላኛው ሰው ገድሎ የሚፎክርን ግለሰብ አንስቶ በሽልማት ይንበሸበሻል-የፎቶ ጋዜጠኝነት ዋጋ!!!?
በቱርክ የ 22 ዓመት ጥቃቅን የፖሊስ መኮንን የነበረው ሜቬልት ሜትትስ Altıntaş, የሩሲያ አምባሳደር/ አንድሬ ሪክልሎቭ /ታኅሣሥ 19, 2016 ላይ የግድያ ወንጀል ፈፀመ. በጦርነት ላይ ባለስልጣኖች ከመገደላቸው በፊት ሶስት ሌሎች ሰዎችን አቁስሏል. © Burhan Ozbilici, አሶሴሽንስ ፕሬስ. የአለም ፕሬስ ፎቶ የዓመቱ እና የቦታ ዜና, የመጀመሪያ ተሸላሚ.


Monday, May 14, 2018

በትናንቱ ተቃውሞ 55 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል

የእስራኤል ወታደሮች 55 ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞችን ከገደሉ ከአንድ ቀን በኋላ ፍልስጤማውያን ለተጨማሪ የተቃውሞ ሰልፍ እየተዘጋጁ ነው።
ዛሬ እስራኤል እአአ በ1948 ከተመሰረተች 70 ዓመት ታስቆጥራለች። ፍልስጤማውያን ይህን ቀን 'ናክባ' ወይም መቅሰፍት ሲሉ ይጠሩታል።
ትናንት የተገደሉት ፍልስጤማውያን የቀብር ስነ ስርዓታቸው ዛሬ ጋዛ አካባቢ የሚፈጸም ሲሆን በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት ይነግሳል ተብሎ ይጠበቃል።

Sunday, May 13, 2018

በጀርመን ቡንደስሊጋ ሀምበርግ እግርኳስ ክለብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለተኛው ዲቪዚዮንን ተቀላቀለ፡፡


በጀርመን ሀምበርግ እግርኳስ ክለብ ቡንደስሊጋው ከተጀመረ ከ1963 እ.አ.አ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለተኛ ዲቪዚዮንን ተቀላቀለ፡፡
ሀምበርግ እግርኳስ ክለብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቡንደስሊጋ ወረደ

የመጨረሻ ጨዋታቸውም ደጋፊዎች ወደሜዳ በወረወሩት ቀይ ነበልባል እና ከተቃራኒ ቡድን ጋር በፈጠሩት ግርግር 15 ቂቃዎች እየቀሩት ተጠናቋል፡፡ 

Saturday, May 12, 2018

ኮከቦቹ ስለ ሮናልዲኒሆ ጎቾ ምን አሉ?


ስለ ራሱ #ሮናልዲኒሆ
ፈጣሪ ለሁሉም ፍጡር ስጦታ ሰጥቷል አንዳንዱ እንዲፅፍ አንዳንዱ እንዲደንስ አንዳንዱ ደግሞ የሰው ልጆችን የማዳን ጥበብ እኔ ደግሞ እግር ኳስ እንድጫወት ተሰጥቶኛል ከነዛ ከስጦታዎች ሁሉ የላቀው ስጦታ ለኔ ፈጣሪ ሰጠኝ!!!





#ዲያጎ_ማራዶና ለእኔ ሮናልዲኒሆ በእግር ኳስ ታሪክ ትልቁ ምልክት ነው። እንደሚመስለኝ በእኔ አመለካከት 2003 – 2005 የነበረው ሮናልዲኒሆ  ሊዬ ሜሲ እና ሲአር 7/CR7/ እጅግ በጣም የገዘፈ ተጫዋች ነበር በእረግጥ CR7 እና Messi ብዙ ጎሎችን ስላስቆጠሩ

Thursday, May 10, 2018

የንስር አሞራ ሚስጥራዊ ተፈጥሮ

ፍጥረታት ሁሉ ይችን ምድር ሲወርሱ የተሰጣቸው አስገራሚና ልዩ ውብ ተፈጥሮ አላቸው፡፡ ከነዚህ የተፈጥሮ ፀጋ ከተሰጣቸው ድንቅ የምድራችን ፍጥረታት መካከል አንዱ የንስር አሞራ ነው፡፡ የንስር አሞራ ምድቡ ከአእዋፍ ወገን ሲሆን ተፈጥሮ የሰጠችው ድንቅ ሚስጥራዊ ተፈጥሮ ግን የተለየ ያደርገዋል፡፡
                                                                                                                     ፎቶ:ከኢንተርኔት
 ዛሬ በዓለማችን የሰው ልጆች አማካኝ የዕድሜ ጣሪያ 65 ዓመት በሆነበት ዘመን ንስር አሞራ ከአዕዋፋት ዘር 70 ዓመት የመኖር ፀጋ ተፈጥሮ የቸረችው የእድሜ ባለጸጋ ነዉ። አስገራሚው ነገር ይህ ድንቅ አእዋፍ ዕድሜው 40 ሲሆን ተፈጥሮ ሁለት አማራጮችን በፊቱ ታቀርብለታለች፤ እንደ አማረበት መሞት ወይም እድሜውን  ወደ 70 አመት ከፍ ለማድረግ ተፈጥሮ ያዘጋጀችለትን የመከራና የስቃይ ጽዋ ምሬት አጣፍጦ በመጎንጨት ተጨማሪ የ30 ዓመት የድል ዋንጫ መቀዳጀት፡፡