Sunday, May 27, 2018

ሳይነስን ለማከም 5 ቀላል መንገዶች …

በሳይነስ ለተሰቃዩ ሰዎች ይድረስ… ሼር አድርጓቸው፡፡

ሳይነስ – በሰውነታችን ውስጥ ያሉ አየር የሚንሸራሸርባቻን ክፍሎች የሚያጠቃ የህመም ዓይነት ነው፡፡

ህመሙ ሶስት ደረጃዎች ያሉት ሲሆን፣ አኪዩት፣ሰብ አኪዩት እና ክሮኒክ ሳይነስ(ሲኖሳይተስ) በመባል ይታወቃሉ፡፡


የህመሙ መነሻዎች የቫይረስና ባክቴርያ ኢንፌክሽን ሲሆን፣አልፎ አልፎ የሰዎች አፈጣጠር ወይም አናቶሚ ለህመሙ መከሰት ሰበብ ይሆናል፡፡

ከሁሉም በላይ ግን ለበሽታው መከሰት ምክንያት እየሆነ ያለው አለርጂ ነው፡፡ይህም አለርጂክ ሳይኖሳይተስ በመባል ይታወቃል፡፡

ይህንን ህመም ለመከላከል የሚጠቅሙ 5 ቀለላልና ተፈጥሮአዊ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. ቀይ ጥሬ ሚጥሚጣ፡-ቃጠሎን መቋቋም እስከቻሉ ድረስ ሳይኖሳይተስን ለማከም ወደር የማይገኝለት ተፈጥሮአዊ መድሃኒት ነው፡፡

አፍንጫን በፍጥነት በማጽዳት ውስጡ ላይ ያለን እብጠት በማጥፋት እፎይታን ይሰጣል፡፡በሚመቾት መንገድ አዘጋጅተው መጠቀም ይችላሉ፡፡

2. ዕርድ፡- ዕርድ በውስጡ ከርከሚን የሚባል እብጠትና የመለብለብ ስሜትን ሚከላከል ንጥረነገር አለው፡፡

ይህ ንጥረነገር ሳይኖሳይተስን ከመከላከሉም በተጨማሪ የሰውነትን የበሽታ መከላከል አቅም ከፍ ያደርጋል፡፡

500mg የእርድ ዱቄትን በውሀ በማዋሀድ ወይም በእንክብል መልክ በቀን ሁለት ጊዜ መውሰድ ጠቃሚ ነው፡፡

3. ነጭ ሽንኩርት፡-ነጭሽንኩርትን በብዛት መመገብ እጅግ በርካታ የጤና ትሩፋቶችን ያስገኛል፡፡

በውስጡ አሊሲን የተሰኘ ንጥረነገር የያዘ ሲሆን፣ይህ ንጥረነገር ቫይረስ ፣ባክቴርያና ፈንገስን የሚከላከል በመሆኑ ለሳይኖሳይተስ ኢንፌክሽን ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡

በቀን ውስጥ ከሁለት እስከ ሶስት ራስ ፍሬሽ ነጭ ሽንኩርትን በማንኛውም ዓይነት መመገብ ከፍተኛ ውጤት ያስገኛል፡፡

4. ቀረፋ፡-በውስጡ ጎጂ የሆኑ ሳይኖሳይተስን የሚያስከትሉ ባክቴርያዎችን የሚገድል ኬሚካል ስላለው ከግማሽ የሻይ ማንኪያ እስከ አንድ የሻይ ማንኪያ ድረስ ከወለላ ማር በመቀላቀል በአንድ ብርጭቆ ለብ ያለ ውሀ መጠጣት ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡

5. ዝንጅብል፡- ዝንጅብል በውስጡ ፀረ-የአፍንጫ ፈሳሽ እና ፀረ-መለብለብና እብጠት ኬሚካሎችን በውስጡ ስለያዘ እንዲሁም የሰውነትን የበሽታ መከላከል አቅም ስለሚጨምር ሳይኖሳይተስን ለመከላከል ይረዳል፡፡

የዝንጅብል ሻይን ከሎሚ ጭማቂ ጋር ቀላቅሎ መጠቀም ለሳይኖሳይተስ ፍቱን መድሃኒት ነው፡፡

6. በሳይነስ ለተሰቃዩ ሰዎች ይድረስ… ሼር አድርጓቸው፡፡

ምንጭ፡-Getutemesegen24.com, `STICETHIOPIA` and `ናቹራል ኪዩርስ ኤንድ ናቹራል ሬሜዲስ ዶት ኮም`

No comments:

Post a Comment