በቱርክ የ 22 ዓመት ጥቃቅን የፖሊስ መኮንን የነበረው ሜቬልት ሜትትስ Altıntaş, የሩሲያ አምባሳደር/ አንድሬ ሪክልሎቭ /ታኅሣሥ 19, 2016 ላይ የግድያ ወንጀል ፈፀመ. በጦርነት ላይ ባለስልጣኖች ከመገደላቸው በፊት ሶስት ሌሎች ሰዎችን አቁስሏል. © Burhan
Ozbilici, አሶሴሽንስ ፕሬስ. የአለም ፕሬስ ፎቶ የዓመቱ እና የቦታ ዜና, የመጀመሪያ ተሸላሚ.
ለካርተር ሞት ያጎናፀፈውን ፎቶ …
ጋዜጠኛው ኬቨን ካርተር ልቡን በማደንደን ያነሳው ፎቶ ግራፍ የዝናን ጥግና የህይወቱን ፍፃሜ ቸረው።
1985 ላይ በሱዳን በነበረው ሁለተኛው የእርስ በርስ ጦርነት ዜጎች ለከፍተኛ ረሃብና መፈናቀል ተጋለጡ። በዚህም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጊኤያዊ የምግብ እርዳታና መጠለያ በደቡብ ሱዳኗ አዮድ ውስጥ ያዘጋጃል።
ጋዜጠኛው ካርተር ደግሞ ወደ ደቡብ ሱዳን ያቀናል ፣ በመንገዱም ላይ ወደ መጠለያው ለመድረስ በመጓዝ ላይ ሆና ከላይ በምስሉ የምትታየው ረሃብ ያጠቃት ትንሽ ልጅ መንገድ ላይ አንገቷን ደፍታ ተቀምጣለች። ከጀርባዋ ደግሞ ጥንብ አንሳ በማረፍ በህይወትና በሞት መሃል ያለችዋን ህፃን ይጎመጃል።
ካርተር ትዕይንቱን ከአስር ሜትር ላይ ሆኖ አሞራው ደንብሮ እንዳይበር በመጠንቀቅ በካሜራው አስቀረው።

ይህ ፎቶግራፍ በኒዮርክ ታይምስ ላይ ታተመ፣ ብዙም አነጋገረ። ካርተር ለዚህ ስራው ከፍተኛውን የጋዜጠኝነት ሽልማት"
Pultizer Award " አሸናፊ ሆነ። ክሶች በረቱ። ይህ ጋዜጠኛ ባሳየው ኢ-ሰብአዊነት፣ የልጅቷን ጉዳይ የተለየ ነገር የለውም በሚል ችላ ብሎ ለነፍስ አድን ሰራተኞች ባለማሳወቁ ተወገዘ።
ኒዮርክ ታይምስ በወቅቱ በልዩ እትሙ ብዙዎች የልጅቷን እጣ እንደጠየቁ ገልፀው ጥንብ አንሳው ከተባረራላት በኃላ ልጅቷ ጉዞዋን መቀጠሏንና ማገገሟን ገልፆ ወደ እርዳታ ማእከሉ ለመድረሷ ግን የሚታወቅ ነገር አለመኖሩን አስታውቆ ነበር።
ካርተርም ሽልማቱን ካገኘ ከአራት ወራት በኃላ ራሱን አጠፋ።
No comments:
Post a Comment