Wednesday, April 25, 2018

በስፔን 90 ኩንታል ኮኬይን ተያዘ

በስፔን አልጀሲራስ ወደብ ሪከርድ በሆነ መጠን 90 ኩንታል የኮኬይን ዕፅ መያዙን የጉምሩክ ኃላፊዎች አስታወቁ፡፡
ኮኬይን እየሸጋገረ የነበረው ትልቅ ኮንቴነር የጫነ መርከብ ሲሆን፥ በሙዝ መያዣ ሳጥኖች ውስጥ ተደብቆ እንደነበረ ተገልጿል፡፡
ኮንቴይነሩን የያዘው መርከብ የተነሳው ከደቡብ አሜሪካዋ ኮሎምቢያ ቱርቦ ወደብ ነው ተብሏል፡፡
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ እስከአሁን ሁለት ግለሰቦች ከፈረንሳይ አራት ደግሞ ከስፔን ተይዘዋል በጥቅሉ ስድስት ሰዎች መያዛቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡


ከዚህ ቀደም በታህሳስ ወር ላይ በዚሁ ወደብ 60 ኩንታል ኮኬይን መያዙ ይታወሳል፡፡
አልጀሲራስ በሜዲታሪያ የሚገኝ ትልቅ ወደብ ሲሆን ለአውሮፓና ለመካከለኛ ምስራቅ ሀገራት እንደሸቀጥ መሸጋገሪያና ማራገፊያ በመሆን የሚያገለግል ማዕከል ነው፡፡

ምንጭ፦ ሮይተርስ

No comments:

Post a Comment