Wednesday, April 25, 2018

የቫይታሚን ዲ እጥረት እና የስኳር በሽታ ተጋላጭነት

ባሳለፍነው ሳምንት የተሰራ አዲስ ጥናት የቫይታሚን ዲ እጥረት ያለባቸው ሰዎች ለስኳር በሽታ የመጋለጥ አድላቸው ከፍተኛ መሆኑን አመልክቷል።
በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ሳንዲያጎ የጤና ኮሌጅ የተካሄደው ጥናቱ ለስኳር በሽታ ያልተጋለጡ እና በስኳር በሽታ የተያዙ አዋቂዎችን ተመልክቷል።


በጥናቱ ላይም 903 ሰዎች የተካፈሉ ሲሆን፥ ለ10 ዓመታት ገደማ ክትትል ከተደረገባቸው በኋላ የተገኘው ውጤት ከሰሞኑ ይፋ ተደርጓል።
በዚህ ወቅትም የተሳታፊዎቹ “25-ሀይድሮክሲ ቫይታሚን” የሚባለው የቫይታሚን ዲ አይነት መጠን የተለካ ሲሆን፥ አጠቃላይ የጤናቸው ሁኔታም ክትትል ተደርጎበታል።

25-ሀይድሮክሲ ቫይታሚን የሚባለው የቫይታሚን ዲ ከፀሀይ ብርሃን የምናገኘው ሲሆን፥ ይህ የቫይታሚን አይነት ለአጥንት እና ለጥርስ እድገትና ጥንካሬ እንዲሁም የተለያዩ በሽታዎችን ለመከላከል የሚረዳ ነው።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2010 ይፋ እንደሆነው መረጃ በአንድ ሰው ደም ውስጥ በአማካኝ በ1 ሚሊ ሊትር ደም ውስጥ 30 ናኖ ግራም 25-ሀይድሮክሲ ቫይታሚን የሚባለው የቫይታሚን ዲ መኖር እንዳለበት ያሳያል።
በዚህም መሰረት በደማቸው ውስጥ 30 ናኖ ግራም 25-ሀይድሮክሲ ቫይታሚን የሚባለው የቫይታሚን ዲ ያለ ሰዎች ለስኳር በሽታ የመጋለጥ እድላቸው አንድ ሶስተኛ መሆኑ ተለይቷል።
በደማቸው ውስጥ 30 ናኖ ግራም በታች ቫይታሚን ዲ ያላቸው ሰዎች በከፍተኛ ደረጃ ለበሽታው የተጋለጡ ሲሆን፥ 50 ናኖ ግራም እና ከዚያ በላይ ያላቸው ደግሞ ከስኳር በሽታ የመያዝ እድላቸው አነስተኛ ነው ተብሏል።
በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የቫይታሚን ዲ መጠንን ከፍ ለማድረግ ደግሞ አሳ፣ እንቁላል፣ ወተት፣ እርጎ፣ የብርቱካን ጭማቂ እና መሰል ምግቦችን ማዘውተር ይመከራል።
ምንጭ፦ www.upi.com/Health

No comments:

Post a Comment